የኦሮሞዎች ለፍትህ፣ ለደህንነት እና ለእውነት (ኦፍደእ) አቋም (ሚያዝያ 25፤ 2016 ዓም)

“ተረኩ: የኦሮሞ መንግስት ተረት አፈጣጠር”

“ትረካው ወደ ላቀ ደረጃ የተወሰደው ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ታዋቂና እና የተመሰከረላቸው ኦሮሞ ጠል ግለሰቦች ነው።
በፀረ ኦሮሞ ንግግሮቻቸው የሚታወቁት መስፍን ወልደማርያም ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ወደር የለሽ የማሰብ ችሎታ ያለው
መለኮታዊ ስጦታ” በማለት ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ አድርገውት ተደመጡ። ኦሮሞንና ቋንቋውን በመጥላት ዝና ያተረፉት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ኢትዮጵያን ለማክበር ሲሉ ራሳቸውን የሰጡ፤ በሺህ አመታት አንዴ ብቅ
ያሉ ድንቅ መሪ” ሲሉ አሞግሰዋቸዋል። ዋና የፖለቲካ ተልእኮውን አዲስ አበባን ከኦሮሞ መከላከል ነው ብሎ የተንቀሳቀሰውና
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መርህ አልባ የፖለቲካ ገፀባሕርይ የሆነው ብርሃኑ ነጋ ደግሞ አብይን “ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመ
እውነተኛ ኦሮሞ” በማለት ገልጾታል።”

“በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን እየመራ ያለው ሀገርን የከዳ ቅጥረኛ መንግስት ነው። የሀገሪቱ ሉዓላዊነት እንዲደፈር ከማድረግም አልፎ የውጭ ኃይሎችን ጋብዞ በአገሪቱ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ወንጀል እንዲፈጽሙ ያደረገ ነው። ሐገሪቱ ዛሬ እየተመራች ያለችው የጦር ወንጀሎችን፣ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን፣ የዘር ማፅዳት እና ምናልባትም የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን በፈጸሙ አካላት ነው። ይህ አገዛዝ የሰብአዊ መብት
ጥሰትን በማናለብኝነት የፈፀመ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ታጣቂዎችን በመፍጠር በንጹሐን ላይ ዘግናኝ ጥቃት እንዲፈጽሙ ያደረገ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ላሉ ችግሮች በውይይት የፖለቲካ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ፖለቲካውን በጦረኝነት የቀየረ በዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የተወገዘ ቡድን ነው።”

UMD Media

View all posts