ልደቱ አያሌው መጋቢት 11 2016 ዓ.ም.

“ኢትዮጵያውያን እዚህ ላይ ቆመንና ከስሜታዊነት ወጣ ብለን ከዚህ በታች የቀረቡትን አምስት አንኳር ጥያቄዎች እንደ ትውልድ ራሳችንን መጠየቅ አለብን።
1ኛ. ጦርነት ለችግራችን ዘላቂ መፍትሄ እንደማያመጣ ለማወቅ ሌላ ስንት ዓመት መዋጋት ያስፈልገናል?
2ኛ. በጦርነት አንዳችን ሌላችንን በዘላቂነት ማሸነፍ እንደማንችል አምነን ለመቀበልና ለሃቀኛ ድርድር ለመቀመጥ ሌላ ስንት ሚሊዮን ዜጐቻችን ማለቅ አለባቸው? ስንትስ የአገር ሃብትና ንብረት መውደም አለበት?
3ኛ. እንደ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትውልድ አባልነታችንስ አገሪቱን ከጦርነት አዙሪት ማውጣት ካልቻልን ካለፈው ትውልድ የተሻለ ለልጆቻችን የምናወርሰው ምን አዲስ ታሪክና እሴት ይኖረናል?
4ኛ. የአገር ህልውናንና የህዝብን ደህንነት ከኛ የጥላቻ ስሜትና የስልጣን ጥያቄ አብልጠን ማየት እንዴትና ለምን ተሳነን?
5ኛ. አብዛኛው የዓለም ህዝብ ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ እየፈታ በሚገኝበት በአሁኑ ዘመን እኛን ከጦርነት አዙሪት እንዳንወጣ ያደረገን መሰረታዊ ምክንያት ምንድን ነው? የስነ-ልቦና መታወክ፣ ወይንስ የማሰብ ችሎታ መቀንጨር? “

UMD Media

View all posts