ልደቱ አያሌው 

ጥር 17 ቀን 2016 ዓ. ም 

በእኔ እይታ በህወሓትና በትግራይ የፖለቲካ ማህበረሰብ ዘንድ በትኩረት ውይይትና ግምገማ ሊካሄድባቸው ይገባል ብዬ የማምንባቸው ጥያቄዎች ከሞላ-ጎደል የሚከተሉት ናቸው። 

 1. አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የገባችበት የፖለቲካ ቀውስ በምን ደረጃ ይገለፃል? ለምንስ ወደዚህ ዓይነቱ ቀውስ ውስጥ ገባች? ለዚህ ቀውስ መፈጠር የትግራይና የህወሓት ልሂቃን ድርሻ ምን ነበር? 
 2. ህወሓት አስካሁን ያራመደው ግራ-ዘመምና ብሔር-ተኮር የፖለቲካ መስመር ምን ውጤት አምጥቷል? ምንስ ጉድለት ነበረበት? 
 3. ህወሓት የኢትዮጵያንና የትግራይን ያለፈ ታሪክ በተመለከተ ያራምድ የነበረው አቋምና ትርክት ምን ጉድለት አለበት? 
 4. ህወሓት የኢትዮጵያን አንድነት፣ የኤርትራን ጥያቄና የባህር-በር ጥያቄን በተመለከተ ያራመደው አቋም ምን ያህል ትክክል ነበር? 
 5. ህወሓት “የአማራ ገዢ መደብ”፣ “ነፍጠኛ”፣ “ትምክህተኛ” በሚሉ ፍረጃዎች ያራመዳቸው ትርክቶች በትግራይና በአማራ ህዝብ ግንኙነት የፈጠሩት አንደምታ ምንድን ነው? ወልቃይትና ራያ የሁለቱ ህዝቦች የቅራኔ ቦታዎች ለምን ሆኑ? ይህ እንዲሆን የህወሓት ሚናና ድርሻ ምን ነበር? 
 6. ከ29 ዓመት በኋላ ህወሓት የአገሪቱን ህገ-መንግሥት በተመለከተ ምን የአመለካከት ለውጥ አለው? በተለይም የመገንጠል መብት እውቅና ማግኘቱና ቋንቋን መሰረት ያደረገ የፌደራል አከላለል በተግባር መዋሉ የትግራይንም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ በአጠቃላይ ምን ጠቀመ? 
 7. ዶ/ር ዐቢይን የመሰለ ደካማና አደገኛ ሰው በኢህአዴግ ምክር ቤት ተመርጦ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲበቃ በማስቻል ረገድ የህወሓት ሚና ምን ነበር? 
 8. ለሁለት ዓመቱ የትግራይ ጦርነት መነሳትና በህዝቡ ላይ ለደረሰው እልቂት የህወሓት ድርሻ ምን ነበር? ከዚህ ጦርነትስ ምን ትምህርት ተቀስሟል? 
 9. የኤርትራ መንግሥት ጊዜ ጠብቆ በትግራይ ህዝብ ላይ በቀል እንዲፈጽም ዕድል በመፍጠር ረገድ የህወሓት ሚና ምን ነበር? ኤርትራን በሚመለከት የህወሓት የወደፊቱ አቋም ምን ሊሆን ይገባል? 
 10. ህወሓት ከ50 ዓመት የትግል ተሞክሮና ሂደት በኋላ ለምን የስትራቴጂክ አመራር እጦት ገጠመው? የአመራር ችግሩን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት? 
 11. በትግራይ ሰብዓዊ መብት እንዳይከበር፣ የብዙሃን ፓርቲና የዲሞክራሲ ስርዓት በበቂ መጠን እንዳይኖር፣ ተፅዕኖ የበዛበት የነፃ ገበያ እንዲኖር፣ ህዝቡ ከድህነት ኑሮ እንዳይላቀቅ በማድረግ ረገድ የህወሓት ሚና ምን ነበር? 
 12. በህወሓትና በብልጽግና ፓርቲ መካከል ያለው የወቅቱ ግንኙነት ጤናማና ተገቢነት ያለው ነው? ወደፊትስ በምን አግባብ ሊቀጥል ይባል? 
 13. በአማራና በትግራይ ህዝብ መካከል ያሉት ቅራኔዎች ዘላቂ ሠላምን በሚያሰፍን አግባብ እንዴት ሊፈቱ ይገባል? 
 14. የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ የገጠሙት መሰረታዊ ችግሮች በቅደም ተከተል ምን ምን ናቸው? እንዴትስ በዘላቂነት ሊፈቱ ይችላል? 
 15. ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከምትገኝበት አጠቃላይ ቀውስ እንዴት ልትወጣ ትችላለች? ለመፍትሄው የህወሓት ድርሻና ሚና ምን ሊሆን ይገባል? 
 16. ህወሓት ደርግን በማስወገድ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወቱና በ27 ዓመቱ የኢህአዴግ ስርዓት የመሪነት ድርሻ ይዞ የሰራቸው በጎ ነገሮች ለምን ተገቢ ትውስታና ምስጋና ሳይቸራቸው ቀረ? በመጡት ለውጦች ተጠቃሚ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና የኢህአዴግ አባልና አጋር የነበሩ ድርጅቶች ጭምር እንዴትና ለምን የዚህ “ውለታ ቢስነት” ባህሪ ሰለባ ሆኑ? የሚሉ ናቸው። 

Editor’s Disclaimer

The above opinion piece is written by a contributor and reflects their personal views and perspectives. It does not necessarily represent the views or opinions of the editorial team, publication, or organization behind UMD Media. We believe in providing a platform for diverse voices and opinions, and encourage our readers to engage critically and thoughtfully with the content. As with any opinion piece, the ideas and arguments presented are subject to individual interpretation and debate.

We welcome feedback and constructive discourse on the topics presented in this piece. If you would like to submit a response or share your own perspective, please contact us at [email protected].

Thank you for your continued readership and support.

UMD Media

View all posts