ልደቱ አያሌው መጋቢት 21፤ 2016 ዓም

“ከረጅም ጊዜ የትግል ልምዴ በመነሳት በእርግጠኝነት ልናገር የምችለው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካለፉት 32
ዓመታት በተለየ መተባበርና መደማመጥ ከቻልን፣ ከአሉባልታና ከሴራ ፖለቲካ ራሳችንን በማራቅ ፈጠራ
የታከለበት አዲስ ሃሳብን ለመቀበል ከተዘጋጀን፣ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ብቻ ይህንን ከህዝብ የተነጠለ
ደካማ አገዛዝ ማሸነፍ እንደምንችል ጥርጥር የለኝም።
የወቅቱ ትግል ለስልጣን የበላይነት የሚካሄድ የፖለቲካ ትግል አይደለም። በህልውና ለመቀጠል የሚደረግ
የሞት የሽረት ትግል ስለሆነ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ የሚተው አይደለም። ለዛሬ ያልሆነ አገርና ህዝብ
ወዳድነት ትርጉም የለሽ ነውና ተፅዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ የሆናችሁ ምሁራን፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ሲቪክ
ማህበራት፣ ባለ ሀብቶች፣ አርቲስቶች፣ ስፖርተኞች፣ ወዘተ… የዳር ተመልካችነትን ትታችሁ የትግሉ ዋና
ተዋናይ መሆን አለባችሁ። ዝና፣ ክብርም ሆነ ባለጸጋነት አገርና ህዝብ ከሌለ ትርጉም የለሽ ነውና።”

UMD Media

View all posts