ደስታ መብራቱ

አዲስ መጽሀፍ

“ከእነኚህ ዓመታት ያገኘሁት ትምህርት ምንም እንኳን ጥቂቶች በፍጹም ቀናነት ለህዝብ መሰረታዊ መብት እና ጥቅም የሚቆሙ ቢኖሩም፣ በጌታ እና ሎሌ መንፈስ ከተለወሰው ፖለቲካዊ ውርሳችን የተነሳ አ ብዛኛዎቹ የፖለቲካ መሪዎች ከምንም በላይ ለጠባብ የግል እና ቡድን ጥቅም የሚሰሩ መሆናቸውን ነው። ይህም በመሆኑ ፣ ከመጨረሻው እስር በተፈታሁበት ወቅት በቀሪው ዘመኔ በሚኖረኝ የትምህርትም ሆነ የሥራ ተሳትፎዬ ከፖለቲካ ለመራቅ ወሰንኩኝ። በዚህ መሰረት ከአንስቶ ስለሃገር በሚደረጉ የተናጠል ውይይቶች ሃሳብ ከመስጠት ያለፈ ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ተሳትፎ አልነበረኝም። ያም ሆኖ፣ ለውጦች በመጡ ቁጥር ሰሚ ሊገኝ ይችላል በሚል ተስፋ ለአዲስ መጪዎቹ መሪዎች ሃሳቤን ከ ማካፈል አልተቆጠብኩም።”

UMD Media

View all posts